ዘባሪቆም

እንግሊዝ ያለሙጋቤ

“…ምን ይሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው፣ለወሬ አይመቹም ተንኮለኞች ናቸው…”

ሰሞኑን ከወደ እንግሊዝ የተሰሙ ግርምትና ጥያቄ አጫሪ ዜናዎች ይህን ቀደምት ስንኝ ቢያስታውሱኝ ወጌን በሱ ልጀምር ወደድኩ።

በመጀመሪያ ቪክቶሪያና አልበርት የተባለ አንድ የለንደን ሙዚዬም “ከሃገረ ኢትዮጵያ የዘረፍኳቸውን ታሪካዊ ቅርሶች ለራሷ ለኢትዮጵያ በብድር ማዋስ እፈልጋለሁ” የሚል መልዕክት አስተላለፈ። በርሱ ተገርመን ሳንጨርስ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ (ከዚህ ንግግራቸው በኋላ ባንዳንዶች ቴሬሳ ‘ጌይ’ ተብለዋል) “ሃገሬ በቅኝ ግዛት ዘመኗ (በተለይ አፍሪካ ላይ) ካደረገችው ሁሉ   ግርምትና ጥያቄ አጫሪ ዜናዎች ይህን ቀደምት ስንኝ ቢያስታውሱኝ ወጌን በሱ ልጀምር ወደድኩ። በመጀመሪያ ቪክቶሪያና አልበርት የተባለ አንድ የለንደን ሙዚዬም “ከሃገረ ኢትዮጵያ የዘረፍኳቸውን ታሪካዊ ቅርሶች ለራሷ ለኢትዮጵያ በብድር ማዋስ እፈልጋለሁ” የሚል መልዕክት አስተላለፈ። በርሱ ተገርመን ሳንጨርስ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ (ከዚህ ንግግራቸው በኋላ ባንዳንዶች ቴሬሳ ‘ጌይ’ ተብለዋል) “ሃገሬ በቅኝ ግዛት ዘመኗ (በተለይ አፍሪካ ላይ) ካደረገችው ሁሉ የሚፀፅታት የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚከለክል ህግ ማሳለፏ ነው” ሲሉ በይፋ ተናገሩ።

‘ሰርቆ ማበደር’ የሚለው የመጀመሪያ ሃሳብ አለማቀፋዊ ባህል ቢሆን የሚበረታታ ነው። አንድ ሌባ የሰረቀውን ንብረት ይፅናና ዘንድ ለባለቤቱ በውሰት የሚያስረክብበት ልማድ ቢፈጠር ሌብነት በስርቆትና ብድር መካከል የሚገኝ ማህበራዊ ክንውን ሆኖ ራሱን ከወንጀልና ሃጢያት ተራ ያሰርዝ ነበር።

 የተመሳሳይ ፆታውን ጉዳይ በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትሯን ንግግር ተከትሎ  “መጽሐፍ ቅዱስን ግብረሰዶም ከሚቃወም ትምህርቱ ጋር ለአፍሪካ ያወረሱት አውሮፓውያን ህጉን ለመሻር ሽንጣቸውን ገትረው ሲታገሉ ማየት ይገርማል”፣ “ግብረሰዶማዊነት በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወይም በቅኝ ገዥዎች ህግ ሳይሆን በአፍሪካውያን ቀደምት ባህል በርኩሰት ተወግዞ የኖረ ምግባር ነው” ወዘተ የሚሉ አስተያየቶች ከያቅጣጫው ተሰንዝረዋል።

የሆነ ሆኖ እንግሊዝ እንዲህ አይነቱን ንቀት የተመላ አባባል ባሁኑ ወቅት ለመሰንዘር ምን አነሳሳት? ብዬ ሳስብ ሁለት ነገሮች ወደ አእምሮዬ መጡ። የመጀመሪያው ይሄ

የ‘Brexit’ ገፈት ራሷ ላይ ወጥቶ እንደ ትኩስ ስካር ሆዷ ያባውን እያስቀባጠራት ይሆን? የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሃይለ ቃልም ቢሆን ጎሸም የሚያደርጓት ፍቱን መድሃኒቷ ሙጋቤና ነውጠኛው ጋዳፊ በመንበራቸው አለመኖራቸው ይሆናል የሚል ነው።

 ለወትሮው በተለይ ግብረሰዶማዊነትን በተመለከተ አዛውንቱ ሙጋቤ እንግሊዝን አፏን ከማስያዝ አልፈው ሲያሸማቅቋት ኖረዋል። በ2015 ZBC ከተሰኘው ያገራቸው ራዲዮ ጋር ባደረጉትና በብዙዎች በሚታወሰው ዝነኛ ንግግራችው “መጀመሪያ ሰውየው በግብረሰዶማዊ ሂደት ተወልዷል ወይ? ብለን እንጠይቃለን፤ እኛ ዝርያችን ለማስቀጠል  

“ለወትሮው በተለይ ግብረሰዶማዊነትን በተመለከተ አዛውንቱ ሙጋቤ እንግሊዝን አፏን ከማስያዝ አልፈው ሲያሸማቅቋት ኖረዋል ”

እንሻለን፣ ያ ደግሞ የሚሆነው በሴቶች እንጂ በግብረሰዶም አይደለም። ጆን ከጆን ማሪያ ከማሪያ ጋር አይሆንም። እነርሱ (እንግሊዝና መሰል አውሮፓውያንን ማለታቸው ነው) ከውሻና አሳማ እንኳን አይሻሉም። እኔ አሳሞች አሉኝ፣ ወንዱ አሳማ ሴቷን ለይቶ ያውቃታል” በማለት አፍሪካውያን ከባህልና እምነታችው ውጪ በአውሮፓውያን የሚታዘዙላቸውን እንዲህ አይነት ‘መጤ መብቶች’ አጥብቀው እንደሚከላከሉ ተናግረዋል።

 የቅርሱን ጉዳይ በተመለከተም እንግሊዝ እውነትም የዘረፈችውን ሁሉ (ያለ ብድር) ብትመልስ እርቃኗን ላለመቅረቷ ዋስትና ማግኘት ይቸግራል። እዚህ ላይ የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙዐመር ጋዳፊ እ.ኤ.አ. በ1989 ከአንድ የኢራን ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ያሉትን ላውሳ። ጋዳፊ በዚህ አስገራሚ ቃለመጠይቅ እንግሊዝ ሌላው ቀርቶ አለኝ የምትለውና የምትኮፈስበት ታላቁ ደራሲ ዊልያም ሼክስፒር ሳይቀር የራሷ እንዳልሆነ ሲናገሩ የሼክስፒር ስራዎች ከአረብ ተረቶች (folktails) የተገለበጡ መሆናቸውን ከመጥቀስ አልፈው ራሱ ሼክስፒር (‘ሼክ’ ስፒር) የዘር ሃረጉ ከአረብ እንደሚመዘዝ በማስረገጥ ጭምር ነው ።

 በነገራችን ላይ በሼክስፒር ስራዎች ባለቤትነት ዙሪያ በራሳቸው በእንግሊዞች ዘንድ ጭምር የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ። አንዳንዶች የሼክስፒር ድራማዎች የፍራንሲስ ቤከን ድርሰቶች እንደሆኑ ሲሞግቱ ሌሎች ክርስቶፈር ማርሎ (Christopher Marlowe) ራሱን እንደሞተ ካደረገ በኋላ በሼክስፒር ስም መፃፉን ይጠቅሳሉ። የሼክስፒር ቀልዶች የሰባተኛው የኦክስፎርድ መስፍን የኤድዋርድ ዲ ቬሬ እንደሆኑ የሚናገሩ፣ ድርሰቶቹን ከንግስት ኤልሳቤጥና ቤተሰቧ እንዲሁም ከሼክስፒር እህት ጋር የሚያገናኙም አሉ። ከነዚህ ሁሉ ሚዛን የሚደፋው ግን ስራዎቹ አንድ ሰው ብቻውን ሊሰራቸው የማይቻለውና በህብረ- ደራሲያን የተሰሩ እንደሆኑ የሚጠቁመው መላምት ነው።

ወደ ዋና ሃሳቤ ስመለስ ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት እንደ ሙጋቤና ጋዳፊ ልካቸውን የሚነግር የአፍሪካ ተቆርቋሪ ከሌለ እንግሊዝና መሰሎቿ በዚህ አይነቱ ሃፍረተ-ቢስ ንግግራቸው የሚረጩት መርዝ ከኒውክሌርና ኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ተለይቶ የማይታይ አህጉራዊ ጅምላ ጥቃት ይሆናል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top