የታዛ ድምፆች

ወጋየሁ ንጋቱ የቴያትር ፈርጥ

አባትና እናቱን ያጣው ገና በልጅነቱ ነው፤ ወንድምና እህት የለውም። ሆኖም፣ በትወና ጥበቡ የብዙ ኢትዮጵያውያን ወንድምና ልጅ ነበር። ችሎታው የሚፈቅድለትን ያህል የብዙዎቻችንን ሕመም ሲታመም፣ ቁስላችንን ሲቆስል፣ ችግራችንን ሲቸገር የነበረ የመድረክ ፈርጥ ነው፤ ነበር – ተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱ።

 ወጋየሁ ንጋቱ፣ ባለትልቅ ተሰጥኦ መሆኑን ለማስረዳት ብዙ መተንተን አያስፈልግም። ሆኖም በረዥም ጊዜ የትምህርት ቤት ክትትል ሊገኝ የማይችል የቴያትር ጥበብ በአጭር ጊዜ የተገለጠለትና ለብዙ ሰዎች የተሰወረውን የዕውቀት ብርሃን የጨበጠ ነበረ። ይህንንም በመድረክና በሬዲዮ ከተጫወታቸው ድራማዎች መዝኖ መረዳት ይቻላል። ይህ ወጋየሁ የሚለካበት ሚዛን ግን በተጫወታቸው ቴያትሮች ሁሉ ሕይወታችንን ቁልጭ አድርጐ የሚያሳይ መስተዋትም ጭምር ነው።

 እርግጥ ነው፣ ስለወጋየሁ ስናነሳ ብዙ ትዝ የሚሉን ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። በነጋሽ ገብረማርያም “የድል አጥቢያ አርበኛ” እና “የአዛውንቶች ክበብ” ፤ በመንግስቱ ለማ “ፀረ ኮሎኒያሊስት” ፣ በፀጋዬ ገብረ መድህን “እናት ዓለም ጠኑ” እና “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” ፣ በመላኩ አሻግሬ “አንድ ጡት” ፣ በማሞ ውድነህ “አሉላ አባነጋ” ፣ በተስፋዬ ገሠሠ “ፍርዱ ለእናንተ” ወዘተ. ቴያትሮች ውስጥ መልኩን እየለዋወጠ በተጫወታቸው ገፀባሕሪያት መታወሱ አንደኛው ነው።

 ዳሩ የወጋየሁ መልክ ምን ይመስል ነበር? ብዙዎቻችን አብዛኛውን ጊዜ ያየነው በመድረክ ላይ እንዳልሆነ ብናውቅም ባስታወስነው ብቻ ሳይሆን ባየነውና ባስተዋልነው ቁጥር ከእርሱነቱ ይልቅ በገፀባሕሪያቱ በዓይነ ሕሊናችን ይታየናል።

 ወጋየሁ ንጋቱ እንዴት የተዋጣለት ተዋናይ ሊሆን እንደቻለ “ዜና ቱሪዝም” በአንድ ወቅት ላቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “… የስቴጅ ዓይኔን የከፈተው … ተስፋዬ ገሠሠ ነበር። የድራማ መምህሬ፤ የተውኔት አባቴ እርሱ ነው” ሲል መልሷል። ተስፋዬ ገሠሠን በስልክ ሳነጋግራቸው እርሳቸው ባዘጋጇቸው ቴያትሮች በ“ሮሚዮና ዡልየት”፣ ፀረ ኮሎኒያሊስት” እና የበጋ ሌሊት ራዕይ” ውስጥ እንደተካፈለ፤ ከእርሳቸውም ጋር ለጊዜው ባስታወሷቸው በ“ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” እና “አሉላ አባነጋ” መጫወቱን ገልጸውልኛል።

 ዘነበ አብርሃ “የመድረኩ ኮከብ” በተሰኘ ርዕስ ስለ ወጋየሁ ንጋቱ ሲጽፍ “ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁትም ቀልቤን የወሰደውም የታዋቂውን ባለቅኔ የፀጋዬ ገ/መድህንን “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” ቴያትር ሲሰራ ነው። ወጣትነቱም አይሎ ነው መሰል ዕንባዬን መግታት ተሳነኝ። ደግነቱ አዳራሹን የሞላው ታዳሚ ሁሉ ይነፈርቃል” በማለት ወጋየሁ በአቡነ ጴጥሮስ ተመስሎ ሲጫወት የፈጠረበትን ስሜት ይገልጻል። ወጋየሁ እንደዚህ ነው።

በመሠረቱ ወጋየሁ በገጸባሕሪይ መረጣ እምብዛም የሚጨነቅ አልነበረም። አልታዬወርቅ ዘለቀ ባዘጋጀችው የሕፃናት ቴያትር (ዲምቱ በከተማ) አንዳንድ ተዋንያን የልጆችን ነገር በመናቃቸው ችግር እንደገጠማት ገልጻ በጣም የታወቀው ወጋየሁ ንጋቱ ግን ከትልልቆች ይልቅ የትንንሾቹ እንደሚከብድ፣ እርሱም በዚህ ተውኔት ለመካፈል ዝግጁ መሆኑን እንደገለጸላት በኢትዮጵያን

“ራስን ረስቶ ገፀባሕሪውን ፍጹም ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል። ሠዓሊና ደራሲ በብዕራቸውና በቡርሻቸው የሚያዩትን ለመግለጽ የሚጥሩ ከሆነ ተዋናይ ደግሞ በራሱ፣ በአካሉ፣ በስሜቱ፣ በመንፈሱ መስሎ መገኘት ይኖርበታል”

ሔራልድ የባህል መድረክ ተናግራለች። “በጣም የሚገርመኝ ከመድረክ ውጭ ሳየው ጭብጥ ይልብኛል። አንዳንድ ጊዜም ኩፍ ያለች ዶሮ መስሎ የሚታየኝ ጊዜ አለ። በዚያው በመድረክ ግን ሲያስፈልገው ስፖርተኛ፣ ሲያስፈልገው ተወዛዋዥ፣ ሲያስፈልገው እንደ መኳንንት ተንጐማላይ ወይም እንደኔቢጤ መሆን ነው” ሲል የሰማሁት አንድ ታዳሚ የተናገረው ምንጊዜም ትዝ ይለኛል።

ዛሬ ለሰው የተሰራው ሰው በነበር የሚታወስ ሆኗል። ከእኛ ጋር በሕይወት በነበረበት ጊዜ ግን የግሉ ተሰጥኦ የሆነ ዕውቀቱን እንኳን ለሚቀበሉ ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነበር። በ1967፣ በ1969 እና በ1970 ዓ.ም. ብሔራዊ ቴያትር በሰጠው የተዋንያን ሥልጠና አስተማሪ በመሆን የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ አበርክቷል። ከተማሪዎቹ ውስጥ እነሲራክ ታደሰ፣ ዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ ተክሌ ደስታ፣ መዓዛ ብሩ፣ ዓለምፀሐይ በቀለ፣ ዓይናለም ተስፋዬ፣ ኃይሉ ብሩና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

 ለብሔራዊ ቴያትር የሰጠው አገልግሎት በዚህ የሚያበቃ አይደለም። ሲጫወት አይተው የመረጡት የሥራ ጓደኞቹ ብቻ ሳይሆኑ በምንጊዜም “እሺ” ባይነቱ የሚጠቀሙና ጠይቀው ለመረዳት የሚፈልጉት ሁሉ ነበሩ።

ኃይሉ ጸጋዬ በጥር ወር 1979 ዓ.ም ስለተስፋዬ ሳህሉ በየካቲት መጽሔት ላይ ሲጽፍ ካነጋገራቸው ሰዎች መካከል አንዱ ወጋየሁ ንጋቱ ነበር። እርሱም እንደ አንዳንድ ሰዎች ሳይኩራራና የምቀኝነት መንፈስ ሳያጠቃው ‹‹ጋሽ ተስፋ ትራጄዲም ኮሜዲም መጫወት ይችላል። ኮሜዲ በሚጫወትበት ጊዜ ዋና ችሎታው የገጸባሕሪውን ደም፣ ሥጋና አጥንት ወስዶ የራሱ ያደርገዋል፣ ይላበሰዋል። በዚህም የደራሲውን ስራ አጉልቶ ያወጣዋል›› በማለት ምስክርነቱን የሰጠ ዕውነተኛ የኪነ-ጥበብ ሰው ነበር።

 አየህ ተዋናይ ለመሆን ሌትም ቀንም ማለም ያስፈልጋል። ሕልሙም የሕዝቡን ስሜት ለመያዝና ለማርካት ቴያትር አይቶ ለመውጣት እንዲችል ማድረግ ነው። አየህ ሕዝብ ተውኔቱን ለመጫወት አለመቻሉ ብቻ ጥሩ ተዋናይ ሲያገኝ ለማድነቅ ሳያገኝ ሲቀር ለማንቋሸሽ አይችልም ማለት አይደለም። ስለዚህ ራስን ረስቶ ገፀባሕሪውን ፍጹም ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል። ሠዓሊና ደራሲ በብዕራቸውና በቡርሻቸው የሚያዩትን ለመግለጽ የሚጥሩ ከሆነ ተዋናይ ደግሞ በራሱ፣ በአካሉ፣ በስሜቱ፣ በመንፈሱ መስሎ መገኘት ይኖርበታል። ግልጽ ባይሆንም እንኳን ከደራሲው ስሜት ውስጥ ፈልቅቆ ለማምጣት መቻል አለበት…” በማለት ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በአንድ አጋጣሚ ገልፆለታል።

 አንጋፋው ከያኒ ወጋየሁ ንጋቱ በሕይወት ዘመኑ በመድረክ 30፣ በቴሌቪዥን 18፣ በሬዲዮ 46 በጠቅላላ 94 ቴያትሮችን በመጫወትና የህዝብ ልጅ በመሆን ዘመኑን አልፏል።

ኅዳር 6 ቀን 1983 ከጥዋቱ 12 ሰዓት ላይ የአንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ ሕይወት በፀጥታ አለፈች። በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡30 ላይም ነፍስ አልባ ሥጋውም በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በተዘጋጀለት የመቃብር ሥፍራ ላይ አረፈ። አብረውት የኖሩት፣ የሠሩትና በዝና የሚያውቁት ሁሉም በጣም አዝነዋል። ከልብ የሚያውቁት ሰዎችማ “በሙያው እርሱን የሚያክል ሰው ከእንግዲህ ለማግኘት ያስቸግራል” በማለት ማዘን የጀመሩት ገና በጠና ታሟል፤ የሚድንም አይመስለንም የሚል አስተያየት መንፈስ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነበር።

 ለስምንት ወራት ያህል የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የከረመው የዚያ ትልቅ ሰው ባለቤት የሆነችው ወ/ሮ አምሳለ ገነት ይመር እንደነገረችኝ ከሆነ “የልጆቹን ነገር አደራ” በማለት ነበር ይህችን ዓለም በሞት የተሰናበተው። ወደር የሌለው ችሎታውን ለሕዝብ ሲያቀርብ በነበረበት ጊዜ የልጆቹን ጉዳይ በሁለተኛ ደረጃ ይዞ ነበር። ታዲያ የሚያውቀው ሁሉ ቢያዝን የሚገርም አይደለም። ይህ ታዋቂ ሰው ወጋየሁ ንጋቱ ነውና። � �Ĝ2

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top