የታዛ ድምፆች

በታንክ ከሆነ እምቢ፤ በትምህርት ቤት እና በብዙኃን መገናኛ ከሆነ ግን እሺ?

በጦርነት ቅኝ ያልገዟትን አገር፤ የልጆቿን አእምሮና የአኗኗር ዘዬ እራሳቸው በሚጠሉት አሉታዊ ገጽታቸው ሳይታክቱ በመቅረጽ ኢትዮጵያን ቅኝ ያደረጓት መሰለኝ። ዘመቻው ከተጀመረ ቆይቷል። መቶ ዓመት ገደማ ይሆናል። የዘመቱብንም ብቻቸውን አይደለም። በዜግነት የእኛ ወገን የሆኑም አሉበት። ያሉበትም፣ አንዳንዴ ባለማወቅ፤ አንዳንዴ በጎ ፈቃድ ከማጣትና የራሳቸውን ፊደል የቀመሰ ብርቱ ዜጋ በማራቅ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሀገርንና ልብን ለእንግዶች በርግዶ በመክፈት ይመስላል።

“ዘመናዊ” ትምህርትና “ዘመናዊ” ሥልጣኔ የሚል ስም ይዘው በመሪዎቻችን ፈቃድ (በመጀመሪያ በቅንና እና ዓለም ከደረሰበት ልድረስ በሚል ጉጉት) ወደ ሀገራችን የገቡት እንግዶች በተአምራውያኑ ስልክ፣

መኪና፣ ፊልም፣ ሬዲዮ ወዘተ. ላይ ላዩን እያማለሉና እያስደመሙ፤ ልጁን በከረሜላ አዋቂውን በ“ፈረንጅ አረቄ” እያሳሳቁ በየጉያቸው ግን ቀስ በቀስ፣ ጊዜ ወስዶ ሰብእናችንን የሚሸረሽር ምስጢር ወሽቀው የነበር-የነበር ከመሰለኝ ሰንብቷል። ይህ ወደፊት በጥልቅ ምርምር ፍርጥርጥ ተደርጎ መነገር ያለበት ነው። ታድያ፣ እኒህ እንግዶቻችን፣ ጠቃሚ የቁሳዊ ሥልጣኔ ምርታቸውን ውጤት ትንሽ-ትንሽ እያላሱንና እያለማመዱን ሱስ አስያዙን። ይህ ምርት የሚመረትበትን መንገድ ግን “ዘመናዊ” በተባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሊያስተምሩን ያንን ያህል አልተጉም። ለዚህም በቂ ምክንያት አላቸው። በቁሳዊ ልማት ተራምደዋል፣ ተራቅቀዋል የሚባሉ ሀገሮች ዓቢይ ዓላማ በእውቀታቸው የሚያመርቷቸውን ምርቶች የሚሸጡባቸው ገበያዎችን በዓለም ላይ ማበራከት እና የዜጎቻቸውን፣ የከበርቴዎቻቸውን፣ የጠቢቦቻቸውን እና የሀገራቸውን ዘላቂ ምቾት መጠበቅ እና የበላይነታቸውን ማረጋገጥ ነው። ስለዚህ፣ እኛ እንደ እነርሱ እንድናውቅ ባይተጉ አይገርምም። የሚገርመው ልባቸው እስኪወልቅ እኛ እንደ እነርሱ አዋቂና አምራች እንድንሆን ቢተጉ ነበር።

ለእኛ ሊተጉልን የሚችሉት ቀደምት አባቶቻችን ነበሩ። ነገር ግን፣ እነርሱም ቢሆኑ፣ ከዚህ “ዘመናዊ” ከሚባል ትምህርት እና ሥልጣኔ ቁልፍ ምስጢሮች ጋር አይተዋወቁም። የቻሉትን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ፣ በዘዴ ጭምር ሊተዋወቋቸው ስለፈለጉ ነበር መጀመሪያ ላይ “ቤት ለእምቦሳ!” ብለው በእንግድነት ያስገቧቸው።

ከእንግዶቻቸው ጋር መኖር፣ መላመድ፣ መተዋወቅ እና መንቃት እንደ ጀመሩ አረማመዳቸውን ያጤነ ጠላት “ይህቺ ባቄላ ካደረች …” ብሎ ይመስላል ለሁለተኛ ጊዜ ወረራቸው። መንቃት የጀመሩትን ዜጎቻቸውንም በላባቸው። መንግሥት እንደገና ከቆመም በኋላ የመልሶ መቋቋሙ ስራ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስለነበሩበት በግምት ከ10-15 ዓመታት ብዙ የውጭና የውስጥ ሽኩቻና ትርምስ የነበረበት ጊዜ ይመስላል።

ይህ ጊዜ ለእንግዶቹ የተመቸ ሳይነብር አልቀረም። በ1940ዎቹ መገባደጃ ላይ ግን የእንግዶቹን አዲስ ገጽታ እና እቅድ አጢኖ ማሰብ ተጀምሮ ነበር ማለት ይቻላል። አቶ ሃዲስ ዓለማየሁ፣ “ትምህርትና የተማሪ ቤት ትርጉም” የሚል መጽሐፍ በ1948 አሳትመው ነበር። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስላሉት

በአንድ ዓረፍተ ነገር ደፍረህ ፍንጭ ስጥ ብባል “የሀገራችንን ትምህርት ከሀገራችን እውቀት ጠቃሚውን፤ ከዘመናዊው ትምህርትም በጎ-በጎውን ወስደን እናዘጋጅ!” የሚል ነበር

እላለሁ። መንግስቱ ለማ፣ በእንግሊዝ ሀገር የነበረ ተማሪም፣ በ1940ዎቹ “The Best System of Ideas” በሚል ጽሑፍ እውጭ ሀገር ለትምህርት የተላኩ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው እድገት የሚበጀውን ሁሉ እያሰቡ እንዲማሩ አምርሮ የተናገረው ከአቶ ሃዲስ ሃሳብ ጋር የሚሰናኝ ነበር (እኔ

ካገኘኋቸው ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው። ሌሎችም ይኖሩ ይሆናል)። ይሁን እንጂ የተማሩትን ኢትዮጵያውያን እጁን ዘርግቶ፣ ልቡን ከፍቶ ተቀብሎ ከእነርሱና ከሀገር-በቀል እውቀትና ልምድ ባለቤቶች ጋር በትጋት እየመከረ የሚያስተዳድር መንግስት በሀገራችን ባለመነበሩ እንግዶቹ እግራቸውን እንደልባቸው ዘርግተው ስራቸውን ቀጠሉ፤ የበላይነታቸውን ለማረጋገጥም በተለያየ መንገድ ተጉ።

የ1953ቱን “ግርግር” ተከትሎም አንድ እድል ተከስቶ ነበር። የተከሰተው ግን በአደባባይ ሳይሆን በ“ጓዳ” ነበር (በወቅቱ፣ ጽሑፉ ይፋ አልሆነም ነበር ለማለት ነው)። አቶ ሃዲስ ዓለማየሁ፣ የሀገራችን ትምህርት፣ እድገት እና አስተዳደር ሊይዝ ይገባል ያሉትን መንገድ የሚገልጽ ጽሑፍ ለንጉሡ አቅርበው ነበር። “ኢትዮጵያ ምን ዓይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል?” በሚል ርእስ በ1966 ያሳተሙት ከሞላ

“አርሴ እና ማንቼ፣ ባርሴ እና ማድሬ የሽማግሌውን፣ የአሮጊቱን፣ የወጣቱን፣ የልጁን፣ የባለሥልጣናቱን፣ የ“ምሁሩን”፣ የነጋዴውን፣ የጄኔራልና-የወታደሩን ወዘተ. ቀልብ ባንዴ ስበው የሀገር መነጋገሪያ ርእስ ጭምር ሆኑ። የወጣቶቻችን መቧቀሻ፣ በጩቤ መዋጊያ ሲሆኑ ደግሞ

ያልታሰበ ስራ ለፌደራል ሰጡ።”

ጎደል ለንጉሡ ያቀረቡትን ነበር። የዚህም ጽሑፍ እድል ከፊተኛው የተለየ አልሆነም። ይሄም ለእንግዶቹ

የመስረግ እድል እያሰፋ ሄደ። ከ1966ቱ አብዮት ጋር ተያይዞ የመጣው ርእዮተ ዓለምም አዳዲስ እንግዶችን ጨመረ እንጂ የእኛን ባህልና እውቀት አጢኖ፣ ለእኛ የሚበጀንን አላስተማረም። የሌሎች ሀገሮችን ልምድ በቅሽምና እየበቀነነ (እየቀዳ) ሳለ የፊተኞቹ እንግዶች ስማቸውን ለውጠው “ዲሞክራሲ” እና “ግሎባላይዜሽን” በሚባሉት ፊታውራሪነት ሌሎች ለቁጥር ከሚያታክቱ እንግዶች ጋር ከመንበሩ አነሱት፡፡

አዳዲስ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ለውጦች አስፈላጊነት ይወሳ ጀመር። ስለትምህርትም ብዙ ተወስቷል። ይሄ የተለመደም፣ ሀገርኛውን እውቀትና ልምድ ያስተዋለም ስላልነበረ አያስገርምም። የሚያስገርመው ሌላው-ሌላው ክስተት ነው።

ልቅ የ“አክሽን” የሚባሉ የተኩስና የሽብር (የቫዮለንስ) ፊልሞች በየቪዲዮው ቤት ለኪራይ ተሰለፉ። ልቅ የወሲብ ቪዲዮዎች ሳንቲም ይዞ ለሄደ ሁለት እግርና እጅ ላለው ሰው ሁሉ በየመንደሩ ይታዩ ጀመር። መጽሔቶች ወሲብ በወሲብ ሆኑ። አርሴ እና ማንቼ፣ ባርሴ እና ማድሬ የሽማግሌውን፣ የአሮጊቱን፣

የወጣቱን፣ የልጁን፣ የባለሥልጣናቱን፣ የ“ምሁሩን”፣ የነጋዴውን፣ የጄኔራልና- የወታደሩን ወዘተ. ቀልብ ባንዴ ስበው የሀገር መነጋገሪያ ርእስ ጭምር ሆኑ። የወጣቶቻችን መቧቀሻ፣ በጩቤ መዋጊያ ሲሆኑ ደግሞ ያልታሰበ ስራ ለፌደራል ሰጡ።

ኤፍኤሞች ፈሉ። “ለጋ” ሊባሉ የሚችሉ፣ እንጀራ ፈላጊ፣ የዋሃን ወጣቶች ለወላጆቻቸው ልጅ ስለመውለድ፣ ስለማሳደግ፣ እርሻ ስለማረስ፣ ምርት ስለመሰብሰብ፣ ስለ ባህልና ስነምግባር ወዘተ. ለማስተማር ሰፊ እድል ተቀዳጁ። በተወሰነ ሰዓት ላይ ደወል በመደወል ስርጭታቸው በሚደርስበት ቦታ ያሉት ጫት ቃሚዎች ሁሉ ዱዓውን ባንድ ላይ እንዲጀምሩ በማድረግ የፈጠራ ችሎታቸውን ያሳዩም ነበሩ። በእኛው የብዙኃን መገናኛ፤ በተለይ-በተለይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፤ በከንቱ ምኞት የሚያስጋልቡ አደንዛዥ ፊልሞች በብዛት ይሰራጩ ጀመር። በወቅቱ፣ “እምዬ ‘ROOTS’ በነዚህ መሀከል እንዲሰለፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድባያደርግ ኖሮ ‘ምን ይውጠን፣ የት እንገባ፣ በምናባታችን እንዝናና ነበር!’ ያልን ብዙ ነበርን”። ይህ ወረራ በእቅድ የታወጀ ክተት ይመስላል። ዘመቻው ግን በአደባባይ አልታወጀም። አይታወጅ እንጂ የአፈጻጸሙ “ስኬት” ግን ፈጣንና “አይጣል!” የሚያሰኝ ነበር። በይፋ ባይታወጅም አፈጻጸሙ መጀመሪያ ላይ በኢሚግሬሽን፣ ከዚያ በውልና ማስረጃ፣ በቅርቡ ደግሞ በቫት የታዩትን ይመስላል። ከሶስቱ የሚለየው ትኩረቱ ሀገር ማዳበር ላይ ሳይሆን ሀገር ማክሳት ላይ መሆኑ ነው። ታድያ ከዚህ በላይ የተጻፈውን ሰምተው፣ አባቶቻችን “እኛ በታንክና በመርዝ ጢስ ግፊት ተቀበሉ! ስንባል በቆራጥ ትግል አንቀበልም!!!!! ያልነውን ቅኝ- ግዛትነት፤ እናንተ እቤታችሁ ድረስ በፈቃዳችሁ ካስገባችኋቸው ሬድዮዎችና ቴሌቪዥኖች ተቀብላችኋል!!!!” ቢሉን መልሳችን ምን ይሆናል?

ተጻፈ 1997 ዓ.ም.

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top