በላ ልበልሃ

ከመንደር እስከ አገር

መጽሐፌ ለሦስተኛ ጊዜ እንዲታተም ስጠየቅ፣ በነባሩ የልባስ ሽፋን እንዳይቀርብ አሰብኩ። መጽሐፉ ስብሐት

ገብረእግዚአብሔርን የሚመለከት በመሆኑ፣ መልኩን ለማሳል ከአንድ ወዳጄ ጋር  ተዋዋልኩ። በቀጠረኝ ሰዓት ስደውልለት “ደርሷል” አለኝ።

“የት መጥቼ ልውሰደው?”አልኩት እየጓጓሁ።

“አራት ኪሎ”

“አራት ኪሎ ምኑ ጋ?” ልቤ መደለቅ ጀመረ።

ተወልጄ ያደግኩበት ሠፈር ነውና …

“ፓርላማ ፊት ለፊት አጥሩ ውስጥ ስትደርስ

ደውልልኝ”

  ስሙ ሲጠራ ያራደኝ፣ አራት ኪሎ ፊት ለፊት ስገጥመው እንዴት ያረገኝ ይሆን? ሄድኩ። ሠፈሬ  በአረንጓዴና  በቢጫ ቆርቆሮ ተከፍናለች። ሙሾ ማውረድ ቃጣኝ።

ሠፈር ይሞታል? አዎ!!…

    ሠፈሬ ከፈረሰች (ከአምስት ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው) ፍርስራሿ ላይ ቆሜአለሁ። በአብሮ አደጎቼ፣ በቡና ተርቲመኞቼ፣ በጥዋ ማኅበርተኞቼ፣ በዕድርተኞቼና በዕቁብተኞቼ ፋንታ ሙጃና ባዕድ ተክሎች መሬቱን ወረውታል።

   የተወለድኩበት፣ ያደግኩበትና የጎለመስኩበት ሥፍራ፣ የመረን ተክሎች መተዳደሪያና መራቢያ ሁዳድ ሁኗል። ጭንቅላታቸው እሾህ ብቻ የሆኑ ተክሎች ሲታዩ፣ እንደ ፊጋ በሬ ሳይደርሱባቸው ተንደርድረው ለመውጋት የፈለጉ ይመስላሉ። ቅጠላቸው አለብላቢት የሞላው ዕፆችን ማየት ስድብ የወረሰው ምላስ ያጋጠመን ያህል ስሜት ያስቆጣል። “የነዚህ ሁሉ ተክሎች ዘር የት አድፍጦ ቆየ?”

   መሬት ስትቆጣና ስታቄም የምትፈጥራቸው በቀሎቿ ይመስሉኛል። አንድ ጊዜ ከጋሽ ስብሐት ጋር መንገድ እየሄድን ድንገት ቁጭ ብሎ መንገድ ዳር የበቀለች ትንሽ የወይን ጠጅ አበባ መመልከት ጀመረ። አበባዋ ከእነሁለንተናዋ ከአተር አትበልጥም። ቀናብሎ

 “ያዛት” አለኝ።

“ለምን?”

“እንተክላታለና”

“አረም እኮ ናት አቦይ” አልኩት ኃላፊነቱን በመጥላት።

“አረም ያላት የሰው ልጅ ነው፤ እሷ ለራሷ

“እዚያው አስፓልቱ ጋ ጠብቀኝ፤ እንዳትገባ። አደገኛ ነው። …” የተወለድኩበትን፣ ያደግኩበትን፣ የጎለመስኩበትን ቦታ ሳይሆን ወላጅ እናቴን የተቀማሁ ያህል ተሰማኝ። “ታጭጄ” ሌላ አካባቢ ብከመርም፤ ይቺ መሬት ማህጸኗ የበቀልኩበት ቤቴ አልነበር? ታድያስ? ከመቼው የሚገድሉኝንም ሰዎች አበቀለች? ምን አቂማ? በምን ተቀይማ? ”

አበባ ነኝ ብላ ነው የምታስበው።”

ተሳዳቢ ምላስና ተዋጊ ጭንቅላት ያላቸው ተክሎችስ እራሳቸውን ማነኝ ይሉ ይሆን? ስልኬን አውጥቼ ደወልኩ። ሠዓሊው አነሳ።

“ደረስክ?”

“አዎ …”

“እዚያው አስፓልቱ ጋ ጠብቀኝ፤ እንዳትገባ።

አደገኛ ነው። …”

አከባቢውን ቃኘሁ። አልፎ አልፎ ሙጃዎቹን ተገን ያደረጉ የላስቲክ ቤቶች ይታያሉ። የተወለድኩበትን፣ ያደግኩበትን፣ የጎለመስኩበትን ቦታ ሳይሆን ወላጅ እናቴን የተቀማሁ ያህል ተሰማኝ። “ታጭጄ” ሌላ አካባቢ ብከመርም፤ ይቺ መሬት ማህጸኗ የበቀልኩበት ቤቴ አልነበር? ታድያስ? ከመቼው የሚኮሰኩሱኝንና የሚወጉኝን ተክሎች ብቻ ሳይሆን፣ ምናልባትም የሚገድሉኝንም ሰዎች አበቀለች? ምን አቂማ? በምን ተቀይማ?

“አገር ሲያረጅ እሾኽ ያበቅላል” ይባላል። አባባሉ “ሩቅ” ነው። ያረጀ አገር ካበቀለው እሾኽ ጀርባ ተገን ያደረገውን ሌላ “እሾኽ” ዛሬ የተረዳሁት መሰለኝ። ሁሉም አስፈሪነታቸውን አዋጥተዋል። አሁን ከሳማው፣ ሳማው ከቆንጥሩ፣ ቆንጥሩ ሰውን ለማጥፋት ካቆበቆበው ሰው ጋር ኅብረ-ዝማሬያቸው የገጠመ ነው። ለማስጠየፍና ለክፋት አንድነት አላቸው። ከቅዱስ ተግባርና ምግባር ተቃራኒዎች ናቸው። ኅብረ-ዝማሬያቸው ከቅዱሱ ማኅሌት ጋር አይገጥምም፤ ለሥጋ ብቻ ሳይሆን ለመንፈስም የሚኮሰኩስ በመሆኑ፣ እነዚህን መዋጋት የአባቶቻችን የሥልጣኔ ግብ ነበር። እጓለ ገብረዮሐንስ የተባሉ ፀሐፊ ስለዚህ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፡-

“(… አባቶቻችን) እብሪተኞችን ነገሥታት በግራም በቀኝም እያሳፈሩ በመመለስ የታሪክ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። እውነትን፣ ትክክለኛነትን፣ ፍርድን በመከተል ደህቀ ልቦናቸውን ፈፅመዋል። የአናብስት መፈንጫ ምድረ-በዳ የነበረውን ቤተ-መቅደስ፣ ቤተ- መንግሥት፣ ሐውልት፣ እልፍኝ አዳራሽ እየሰሩ ከትመውበታል። በዙሪያቸው የነበረውን እንደ እሣት ያለውን የሥነ- ፍጥረት ተቃራኒነት አለዝበው ለፍቃዳቸው አስገብረውታል። በአመጽ፣ በተንኮል በየጊዜው የተቃጣውን በሠይፍ በሚገባ በመመከት በርትተው ተከላክለው ከተማውን ችግሩን አልፈዋል። … ይህ ሁሉ ገድልና ጥረት አንድ ዓላማ ነበረው። “ከመይርከቡ ሕይወተ አንተ ይኄይስ” የላቀ የበለጠ ሕይወት ለመኖር፤ ሁል ጊዜ ለመሻሻል እምነት ነበራቸው። በዚህ እምነት እየተመሩ የሥልጣኔን መንገድ ይዘው ወደ ላይ ተጓዙ፡፡ 

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top