ጣዕሞት

ሞሰብ የባህል ቡድን ሀገራዊ ሙዚቃዎችን አቀረበ

ሞሰብ የባህል ቡድን ሀገራዊ የባህል ሙዚቃዎችን በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪዎች በተገኙበት በብሔራዊ ቴያትር ከሰሞኑ አቅርቧል።

በዕለቱም ባቲ፣ አንቺ ሆዬ ለኔ፣ አምባሰል፣ ትዝታ እና ሌሎች የሀገር ባህል የሙዚቃ ስልቶችን ከራስ ፈጠራ ጋር አሰናስለው አቅርበዋል።

በመቀጠልም በሰሜን ጎንደር የሚገኙ ማህበረ-ሰቦች የሚጨፍሩት ባህላዊ የሳንኪ ጭፈራም በሶስት ተወዛዋዦች ቀርቦ የታዳሚዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ ከታዳሚው ከፍተኛ አድናቆትም አትርፈዋል።

እንዲሁም ከደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፍ የተወሰደ አበጀ በለው የተባለ ገፀ-ባህሪን ቀንጨብ አርገው በአንድ ሰው የሚከወን ቴያትርም አቅርበዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top