ጣዕሞት

“ኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ” መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ

በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ የተጻፉ ድርሰቶች በአንድ መድበል የተሠናሠሉበት “ኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ” መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ።

መድበሉ ቀደም ሲል በተናጠል የታተሙ የአቶ መለስ ዜናዊ ድርሰቶች ስብስብ ሲሆን በፖሊሲና ስትራቴጂ አስተዋፅኦዎች፣ በገጠር ልማት ራዕይ፣ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ላይ የሚያተኩር ነው።

“ኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ” የልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ድርሰቶች መድበል 734 ገጾች ያሉት ሲሆን በ599 ብር ዋጋ ለገበያ ቀርቧል።

የአቶ መለስ ዜናዊ ድርሰቶችን በአንድ መድበል አሰባስቦና አሠናሥሎ ለህትመት እንዲውል ያደረገው የመለስ ፋውንዴሽን ነው።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top