ጣዕሞት

“የግጥም ምሽቶች ወደ ማኅበራዊ ፋይዳ እያዘነበሉ ነው”

በየወሩ በሆቴሎች በሚካሄዱ የግጥም በጃዥ ምሽቶች ላይ የሚቀርቡ የሥነጥበብ ሥራዎች ላይ ከጥበብ ለጥበብነትይልቅ፣ ጥበብ ለማህበራዊ ፋይዳ መርህ ጎልቶ መውጣቱን ታዳሚዎች ገለጹ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በነዚህ የኪነጥበባት ዝግጅቶች ላይ የባለሙያዎችንም ሆነ የታዳሚዎችን ቀልብ እየሳቡ የሚገኙ ርዕሰጉዳዮችባለሙያው በራሱ የህይወት መንገድ ከተደመመበት የጥበብውበትይልቅ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሞራላዊና ፖለቲካዊ ምልከታቸው የጎላናህዝባዊ ፋይዳያላቸው ሥራዎች መሆናቸውን አንዳንድ ታዳሚዎች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

በራስ፣ በዋቢ ሸበሌ፣ በኢትዮጵያና በሌሎች ሆቴሎች የሚቀርቡ የኪነጥበብሥራዎች ማኅበረሰቡ በቤተሰባዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በሃይማኖታዊ፣ በሞራላዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አተያይ በሂስ መንገድ የሚያመላክቱመሆናቸውን የሥነጽሑፍ ባለሙያዋ ወ/ሮ ሃና ዓለሙ ገልጸዋል።ዝግጅቶቹንበጥበበኛውና በታዳሚው መካከል የመነጋገሪያ አጀንዳና ከወር እስከ ወር ተናፋቂ ያደረጋቸውም ይኸው ሂስ ተኮር ጥበባቸው መሆኑን ወ/ሮ ሃና ጨምረው ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና፣ ጦቢያ የግጥም በጃዝ ምሽት በራስ ሆቴል አዳራሽ ለ79ኛ ጊዜ ሲካሄድ፤ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ የ‹‹ብሔራዊነት››ን ትርጉም ከአጠቃላይ የሀገራችን ሁኔታ ጋር አነፃፅረውያቀረቡትትንተናከታዳሚውሞቅ ያለ ምላሽ አግኝቷል።

በዕለቱም ፍሬዘር አድማሱ፣ ገዛኸኝ ጸጋውና ነቢይ መኮንን የግጥም ሥራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ ነቢይ እያዋዛ ያቀረባቸው ቁምነገሮች ታዳሚውን ፈገግ አሰኝተዋል።በአርቲስት ሽመልስ አበራና በእታፈራሁ መብራቱ ተዋናይነት የቀረበው አጭር ቴያትርምታዳሚውን ያዝናና ማህበራዊ ሂስ ነበር።

ደራሲ ሚካኤል ሽፈራው ስለሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሥራና ሕይወት አጭር ንግግር ያደረገ ሲሆን፣ በተለይም “ወንድ ወለድሁ”፣ “ቢራቢሮ”ና”እግር እንይ”በተሰኙት የጸጋዬ የግጥም ሥራዎች ላይአተኩሮ ተናግሯል።

የፕሮግራሙ መዝጊያ የነበረው “የባለቅኔው ማስታወሻ”በተሰኘ ርዕስ የቀረበውየበኃይሉ ገ/እግዚአብሄር ወግ ሲሆን ከታዳሚው ሞቅ ያለ ምላሽ አግኝቷል። ጦቢያ በጃዝ ምሽት የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. 80ኛ ዝግጅቱን በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ያቀርባል ተብሏል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top