ጣዕሞት

ኮሜዲያን አለባቸው ተካ ተዘከረ

ሜዲያን፣ ተዋናይናየመድረክ መሪ አለባቸው ተካን የሚዘክር ፕሮግራም በብሔራዊ ቴያትር ተካሄደ። አለባቸው ተካ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቱ
ካለፈ 13 ዓመት ሆኖታል።

በብሔራዊ ቴአትር በተዘጋጀው የኮሜዲያን አለባቸው ተካ መታሰቢያ ዝግጅት ላይ የጥባብ ባለሟሎች ስለ አለባቸው ተካ ሥራዎች ያላቸውን ምልከታ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከአለባቸው ተካ ጋር በጥምረት ለዓመታት የጥበብ ሥራዎችን ይከውን የነበረው እውቁ ኮሜዲያን ልመንህ ታደሰም መድረክ ላይ ወጥቶ የበኩሉን ተጠብቧል።

ጥር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ዝግጅት አንጋፋ የጥበብ ሰዎች፣ የአለባቸው ተካቤተሰቦች፣ ጓደኞቹና አድናቂዎቹ የተሳተፉ ሲሆን ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ በተለያዩ ጥበባዊ ዝግጅቶች ደምቆ ነበር።

በዕለቱ የአለባቸውን የህይወት ታሪክና ሥራዎች የሚገልፅ ዘጋቢ ፊልም የቀረበ ሲሆን፣ የቅርብ ጓደኛው ደራሲና ዳይሬክተር ተስፋዬ ማሞ ስለ አለባቸው ተካ ማንነት አጠር ያለ ንግግር አድርጓል።

ይህን የመታሰቢያ ዝግጅት ያስተባበረው አብ ሐበን የማስታወቂያ ድርጅት ሲሆን፣ “እኛ ኢትዮጵያውያን ጀግኖቻችንን ማወደስ ልማዳችን ማድረግ አለብን” በሚል መሪ ቃል የአለባቸው ተካን የመታሰቢያ ፕሮግራም ማካሄዱን አስታውቋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top