አድባራተ ጥበብ

“ባሩድና ብርጉድ” በዕይታ ላይ ነው

የሠዓሊ፣ ቀራፂ እና መምህር በቀለ መኮንን “ባሩድና ብርጉድ” የጥበብ ዓውደ ርዕይ በጀርመን ባህል ማዕከል ጎተ- ገብረክርስቶስ ደስታ የጥበብ አዳራሽ በመታየት ላይ ነው።

በዓውደ ርዕዩ ላይ የአርቲስት በቀለ መኮንን የቀለም ቅብ፣ ኢንስታሌሽን እና ቅርፃ ቅርጽ የጥበብ ሥራዎች ለዕይታ ቀርበዋል። ዓውደ ርዕዩ ለአንድ ወር ዕይታ ይቆያልም ተብሏል።

አርቲስት በቀለ መኮንን የዓውደ ርዕዩ መግቢያ ላይ እፍኝ ሃሳብ ስለ ‹‹ባሩድና ብርጉድ›› በሚል ‹‹በሰው ልጅና በሚለብሰው ልብስ መካከል ያለው አስገራሚ ግንኙነት እኔንም ያስደንቀኛል፣ ያሳስበኝም ነበር። በተለይ ላለፉት አምስት ዓመታት በደንብ ሳስተውለው ነበር››በማለት ለዚህ ዓውደ ርዕይ መነሻ የሆነውን የቀሳውስትና የወታደር ልብሶች ያላቸውን ሥነልቦናዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች ያመላክታል።

 

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

በብዛት የተነበቡ

To Top