ከታህሳስ 16 – 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው 12ኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል 17 ያህል ፊልሞች ቀርበውበታል። ታህሳስ 16 ቀን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴያትር የተከፈተው ፌስቲቫል “ቀያይ እምቡጦች”ን (Red Leaves) ቀዳሚ አድርጎ ጀምሯል። በባዚ ጌቴ የተዘጋጄውና በቤተ እሥራኤላውያን ታሪክና ኑሮ ላይ የተመሠረተው ይኸው ፊልም አንጋፋ ተዋናይ ደበበ እሸቱ መሪውን ገፀባህሪይ ምስጋናው ታደለን ወክሎ የሚጫወትበት ነው። በፌስቲቫሉ ማጠቃለያ የተመረጡ ኢትዮጵያዊ ፊልሞች በ12 ዘርፎች እንደሚሸለሙ የፌስቲቫሉ ዲሬክተር አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል።
