ከቀንዱም ከሸሆናውም

ፓብሎ ኔሩዳና የአስከሬን ምርመራው

ኔሩዳ የቺሊ ባለቅኔ ነው። በ19 ዓመቱ አስደናቂ ግጥሞቹን ለህትመት አበቃ። በ1927 ዲኘሎማት በመሆን በተለያዩ ሀገራት እየዞረ የፖለቲካ ሥራውን አከናወነ። በስፔን የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ስፔን ውስጥ ነበር። ጦርነቱ ብዙ መራር ትዝታዎችን ጥሎበት አልፏል። በጣም የሚወደው ጓደኛው ፌድሪኮ ጋርሺያ ሎርካ በመሞቱ ውስጡ እጅግ ተጐዳ። በ1945 ስታሊንና ኮሙኒዝም በሚከበሩበትና በሚደነቁበት ዓመት የቺሊ ኮሙኒስት ፓርቲ አባል ሆነ። የተባ ብዕሩን በመጠቀም የቬትናምን ጦርነት አወገዘ። ሶሻሊስቱን የሳልቫዶር አየንዴ መንግሥት በታጋይነት (1970 73) አገለገለ። ፒኖቼ አየንዴን በ1973 ሲገለብጥ ኔሩዳ በፕሮስቴት ካንሰር ህመም ይሰቃይ ነበር። መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ ከ12 ቀናት በኋላ ኔሩዳ እስከ ወዲያኛው አሸለበ። ከመሞቱ አስቀድሞ ግን አንድ ነገር ተናገረ። “አንድ ረዥም፣ ባለ ሰማያዊ ዓይን ዶክተር መርፌ ከወጋኝ በኋላ ነው በሽታው የፀናብኝ” አለ። የዶክተሩም ስም ፕራይስ ነበር።

ዶክተር ፕራይስ የሲአይ.ኤ ወኪልና የፒኖቼ ደጋፊ ነበር። ከዚህ ዶክተር በተጨማሪ ለኔሩዳ መሞት ተጠርጣሪው ከናዚ ጋር ግንኙት የነበረው ጀርመናዊ ዶክተር ሀርለሙት ሆፕ ነው። በ2ዐ13 በተደረገ ምርመራ በመርዝ ለመሞቱ የተገኘ ማስረጃ የለም። በ2ዐ15 ዳግም አስከሬኑ ተመርምሮ ተፈጥሯዊ ያልሆነ ምልክት በአስከሬኑ ላይ አልተገኘም። ሆኖም የቺሊ መንግሥት ውጤት አገኛለሁ በሚል ምርመራውን አላቆመም።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top