ጣዕሞት

“የኢትዮጵያና ጣሊያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ” ለንባብ በቃ

“የኢትዮጵያና ጣሊያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን በሃገር ፍቅር ትንሿ አዳራሽ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል።

መጽሐፉ ታሪካዊ ሃተታ ሲሆን፣ በወቅቱ የነበሩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን፣ መረጃዎችን እና ሠነዶችን በ207 ገፅ አሰናኝቶ በ80 ብር ዋጋ ነው ለገበያ የቀረበው።

መጽሐፉ በተመረቀበት ወቅት የታሪክ ምሁራንና ተመራማሪዎች፣ እንዲሁም የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን፣ ደራሲው አቶ ጥላሁን ጣሰው መጽሐፉ በጊዜው የነበረውን የጦርነትሥልት፣ የንጉሠ-ነገሥቱን የአመራር ዘይቤና ሂደት፣ እንዲሁም በእንግሊዝ አገር ተገኝተው የጣሊያን መንግሥት ከኢትዮጵያ እንዲወጣ የዓለም መንግሥታትን የጠየቁበትን አግባብ፣ ሞሶሎኒ በኢትዮጵያውያን ላይ መርዛማ ጋዝ ስለመጠቀሙ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ማካተቱንም አስረድተዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top