ጣዕሞት

የሰለሞን ደሬሳ ‹‹ሥንብት››

ጎምቱው የፍልስፍና ሊቅ፣ መምህር እና ገጣሚ ሰለሞን ደሬሳ ጥቅምት 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚኖርበት አሜሪካ በሚኒሶታ ክፍለ ግዛት በልብ ህመም ምክንያት በ80 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አስከሬኑ በኑዛዜው መሠረት በበነጋታው ተቃጥሏል።

በጠና ታሞ ሥራውን እስካቆመበት ጊዜ ድረስ በሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ የሃይማኖት ንፅፅርና የፍልስፍና መምህር ሆኖ ሲያገለግል የቆየው ሰለሞን ደሬሳ፤ በሀገር ውስጥ በነበረበት ጊዜ ‹‹አዲስ ሪፖርተር›› የሚባል ጋዜጣ ያሳትም ነበር። ለተለያዩ ጋዜጦችም ይጽፍ ነበር።

በህይወቱ ሶስት መጻሕፍት ለማበርከት እንደሚፈልግ ሲናገር የነበረው ሰለሞን ደሬሳ፣ ‹‹ዘበት እልፊቱ- ወለሎታት›› እና ‹‹ልጅነት›› የተባሉትን ቀደም ሲል ያሳተመ ሲሆን፣ በመጨረሻ ‹‹ስንብት›› ሲል ያሰናዳውን የድርሰት ረቂቅ አውሮፕላን ላይ ጥሎት (ጠፍቶበት) እንደ ወረደ መናገሩ ይታወሳል። ሆኖም፣ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከሌሎች ጋር አንድ መጽሐፍ ማሳተም ችሏል።

ከእናቱ ከወ/ሮ የሺመቤት ደሬሳ፣ ከአባቱ ከአቶ ደሬሳ ላንኪ በቀድሞው የወለጋ ጠቅላይ ግዛት ጊምቢ አውራጃ ውስጥ በምትገኝ ጩታ ቀበሌ የተወለደው ሰለሞን ደሬሳ፣ የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top