ጣዕሞት

አፍሪ ኸልዝ ቴሌቪዥን ሥራ ሊጀምር ነው

ትኩረቱን በጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ያደረገው አፍሪ ኸልዝ የቴሌቪዥን ጣቢያ በቅርቡ በአማርኛ ቋንቋ ሥርጭቱን ሊጀምር ነው። በመቀጠልም በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ፕሮግራሙን ማሰራጨት ይጀምራል ተብሏል።

በስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎችና በባለሃብቶች የተቋቋመ ነው የተባለው ይኸው ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤቱ በመካከለኛው ምሥራቅ ዱባይ ሲሆን ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱንና የፕሮዳክሽን ካምፓኒውን በኢትዮጵያ በማቋቋም ሥራውን እንደሚጀምር ተገልጿል።

በሀገራችን በጤና ላይ ያተኮረ ጋዜጠኝነት እንዲስፋፋ፣ በሕክምናው ዓለምና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ሲሉ መስራቾቹ ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

በህክምናው ዓለም የተገኙ አዳዲስ ግኝቶችን፣ ለጤና ጠቃሚ ምክሮችን፣ በሽታን የመከላከል ዘዴዎችንና አልፎም ማህበረሰቡ ከአደጋ እና ድንገት ከሚከሰቱ የጤና እክሎች ራሱን የሚጠብቅባቸውን መፍትሄዎች ቀላልና አዝናኝ በሆኑ መንገዶች ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን መስራቾቹ ተናግረዋል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top