ከወደ ሰሜኑ ከወደስተ በላይ-
እርቃኑን በቀረው በተራራ ጫፍ ላይ፣
ወፍ ዘራሽ ፅድ ቆሞ ሲታይ-
በረዶውን ለብሶ ጎንበስ ቀና እያለ- ያምራል እንደ
ሰማይ፣
ባለ ግርማ ሞገስ ሽማግሌ መሳይ፤
••• ••• •••
በሌላው አቅጣጫ ራቅ ካለ ቦታ-
ፀሐይ ካለችበት በእጅጉ በርትታ፣
አሳዛኝ ዘንባባ በቅሎ አለ በተርታ፣
አየ ጉድ ያሰኛል፣ አየ ጉድ ተፈጥሮ
በያቅጣጫው ተበትኖ፣ ተስፈንጥሮ።
ገጣሚ፡- ሚሃኤል ሌርሜንቶቭ (1841 ሩሲያ)
ትርጉም፡- አልማዝ ገ/መስቀል (ሩሲያ ባሕል ማዕከል)
