ጣዕሞት

ቅኔ ዘፍልሱፍ በገበያ ላይ ዋለ

የደራሲ ካሣሁን ዓለሙ ቅኔ- ዘፍልሱፍ የተሰኘ መድበል በቅርቡ ለንባብ በቅቷል።

በዚህ መድበል የፍልስፍና መራሄው የተፈጥሮ ቅኔነት፤ የቅኔነት ምሥጢር፣ በተፈጥሮ ውስጥ በኅብርነት፣ በዕምቅነት፣ በዜማ ሰሀቢነት….ተጽፎ ይገኛል ይለናል ደራሲው። መፈላሰፍ ማለትም ይኸን የተጻፈውን ቅኔ አንብቦ መፍታትና ምሥጢራዊ ጥበቡን አውጥቶ (ገልጦ) ማሳየት ነው። በተጨማሪም በዚህ ዘመን ብቅ ያሉትን አምላክ የለሾች በፍልስፍናው ሕግ መሠረት በአመክንዮ እንደሚሞግታቸው ይገልፃል።

ደራሲ ካሣሁን ዓለሙ ከዚህ በፊት መሠረታዊ ሎጂክና ሕፀፅ እንዲሁም ህልዎተ እግዚአብሔር የተሰኙ መጻሕፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል።

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top