ቀዳሚ ቃል

‹‹ታሪኩን፣ ምንጩንና ባህሉን የማያውቅ
ሕዝብ ሥር እንደሌለው ዛፍ ነው››
ማርከስ ጋርቬይ

 ቀዳሚ ቃል  

ውድ አንባቢያን፣

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ! እነሆ “ታዛ” የተሰኘች ወርሃዊ የሥነ ጥበብና የባህል መጽሔታችንን የአዲስ ዓመት ስጦታ አድርገን አቅርበንላችኋል። “ታዛ” ጥላ፣ የቤት ጥግ፣ መጠለያ፣ ማረፊያ እንዲል፤ መጽሔታችንም በሰከነ አእምሮ አረፍ ብለን፣ ጊዜ ወስደን የምንነጋገርባት፣ የምንወያይባት እንድትሆን ምኞታችን ነው። ሥነ ጥበብና ባህል ደግሞ ራሳችንን በውል የምናይባቸው፣ አንድነታችንን የምናፀናባቸው፣ የማንነታችን መግለጫዎች ናቸው። እኛ የታዛ አዘጋጆች በተለይ በዚህ የሉላዊነት ዘመን ወጣቶቻችን መሠረታቸውን ሳይለቁ ወደፊት እንዲራመዱ የማድረግ ሃላፊነት አለብን ብለን እናምናለን። ማንነቱን፣ ምንጩን ወይም መነሻውን የማያውቅ ሰው መድረሻውን ሊያውቅ አይችልምና።

በዚህ እትም ስለቅዱስ ያሬድ ታሪክና ስለ ግዕዝ ሥነጽሑፍ የመስኩ ሊቅ ያዘጋጁትን ጥናታዊ ጽሑፍ ታነባላችሁ። የፖለቲካ ባህላችንን ተኩስ ቃላትን፣ በብዕር ቃታ… ‹‹ታሪኩን፣ ምንጩንና ባህሉን የማያውቅ ሕዝብ ሥር እንደሌለው ዛፍ ነው›› ማርከስ ጋርቬይ ለማረቅ ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ መፍትሄ የለም። ‘ይህን እንዳናደርግ የሚያግደን ምንድን ነው?’ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከኋላ ጀምሮ ያለውን ታሪካችንን የሚቃኝ ጽሑፍም አለን። ሌሎች በርከት ያሉ ርዕሰ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ። አንጋፋው ደራሲ ልምዱን ለተተኪው ያካፍላል። የታዋቂውን ዜማ ፈጣሪ የአበበ መለሰን ሕይዎት የሚቃኝ ቃለ-መጠይቅም ተሰናድቷል፡፡ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ ነንና የጥንቱን የዘመን መለወጫ የሙዚቃ ድግስና ውድድር እያስታወሰ፣ የዚያን ዘመን ትውልድ በትዝታ ወደኋላ የሚወስድ ለወጣቱ ደግሞ ትምህርታዊና አዝናኝ የሚሆን ጽሑፍም ይዘናል።

“ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” እንደሚባለው እንዳይሆንብን ቀሪዎቹንም ሥራዎች ወደ ውስጥ ስትዘልቁ መርምሯቸው። እባካችሁ ፃፉልን፣ ሃሳብ አስተያየታችሁን ላኩልን። የሃገራችንን ሥነ ጥበብና ባህል በጋራ እንወቅ፣ እንጠብቅ፣ እናበልፅግ፣ እናስተዋውቅ። ወጣት ጸሐፍትንም እናበረታታለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ጽሑፍ ያበረከቱልንን፣ አስተያየት የሰጡንንና በርቱ ያሉንን ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን።

መልካም ንባብ!

ትኩስ ቃላትን፣ በብዕር ቃታ…

ትኩስ ቃላትን፣ በብዕር ቃታ…

 

Click to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

To Top